askwala.com - ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለዊንዶዉስ እና ለኦፊስ ምርቶች አዉቶማቲክ የደህንነት ማዘመኛ ስርአት ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን ገለጸ
Header







ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለዊንዶዉስ እና ለኦፊስ ምርቶች አዉቶማቲክ የደህንነት ማዘመኛ ስርአት ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን ገለጸ


ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከመጭዉ ሃምሌ 2022 ጀምሮ ለዊንዶዉስ እና ኦፊስ ምርቶች የሚሆን አዉቶማቲክ የሆነ ማዘመኛ ስርአትን ለደንበኞቹ እንደሚያቀርብ ገለጸ።
ይህ አዉቶማቲክ የሆነ የደህንነት ማዘመኛ ስርአት ለተጠቃሚዎች በነጻ የሚቀርብ ሲሆን የዊንዶዉስ 10 ወይም 11 ተጠቃሚዎች ይህንን አግልግሎት ከሃምሌ ወር ጀምሮ ያገኛሉ ተብሏል።
ይህ አገልግሎት የዊንዶውስ እና የኦፊስ ሶፍትዌርን እየተጠቀሙ ላሉ ደንበኞቹ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ እንደሚቀርቡ የገለጸዉ ኩባንያዉ ስርአቱ አዉቶማቲክ እና በራሱ የሚተገበር የደህንነት ማዘመኛ መሆኑን ገልጿል።
ማዘመኛዉም ወር በገባ በሁለተኛዉ ሳምንት ማክሰኞ የሚቀርብ መሆኑን የማይክሮሶፍት ኩባንያ ከፍተኛ የምርትና እና ማርኬቲንግ ማናጀር የሆኑት ሌዎር ቤላ ገልጸዋል።
ይህ አማራጭ ከዚህ ቀደም የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ እና የኦፊስ ተጠቃሚዎች በማይክሮሶፍት ኩባንያ የሚቀርቡ ወርሃዊ የደህንነት ማዘመኛዎችን እና ክፍተት መሙያዎችን ለመተግበር የግድ ፍቃድ መስጠት እና ሂደቶችን ተከትለዉ የማዘመን ሂደትን የቀየረ ሲሆን የዊንዶዉስ እና የኦፊስ ተጠቃሚዎች ያለምንም ዉጣ ዉረድ የደህንነት ዝመናዎችን መተግበር የሚያስችል ነዉ። 

















Short info

× Chat