በመሆኑም እነዚህ ወሳኝ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች የአገልግሎት አሰጣጥ፣ መዋቅራዊ ኡደትና ስርዓታቸው ደህንነታቸዉ እንዲጠበቅና የአሰራር ሂደታቸው እንዳይስተጓጎል የሚያስችሉ የደህንነት መቆጣጠሪያ አፕሊኬሽኖች ተግባራዊ ይደረጋሉ። ከእነዚህ መተግበሪያዎች መካከል አንዱ የጥቃት መጠቆሚያ ስርአት ነዉ።
የጥቃት ሙከራዎች መጠቆሚያ ስርአት #Intrusion_Detection_Systems ሶፍትዌር ወይም ሃርድዌር አጠቃላይ አዉታረ መረብ ውስጥ ያሉ ስርአቶችን ከመጥፎ ወይም የሳይበር ጥቃት አደጋን ሊያስከስቱ የሚችሉ የበይነመረብ ትራፊኮችን ለመለየት ፣ ለመቆጣጠር እና ሲከሰት ለማሳወቅ የሚያስችሉ የደህንነት ማስጠበቂያዎች ናቸው።
ይህን ተግባር የሚከዉኑት ደግሞ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች በሚሰጧቸው ህግ እና መመሪያ መሰረት ነው።
እነዚህ ቴክኖሎጂዎች አስጊ የሆኑ የጥቃት ክስተቶችን የሚለዩት በውስጣቸው የዳታ ጥቅልን ወይም ፓኬትን ሲግኒቸር እንዲሁም የትራፊኩን ሁኔታ ወይም ባህሪይ በማጥናትና በመመርመር ላይ ሲሆን ከዳታ ቤዛቸው ጋር ካለ መረጃ ጋር በማወዳደር እና ተዛማጅ የሆነ የመረጃ ፍሰትን የሚለዩበት ሴንሰር ወይም መፈተሻ ዘዴ በመጠቀም ነው።
ይህ ስርአት ተግባራዊ ማድረግ የሳይበር ጥቃቶች ከመፈጸማቸዉ በፊት መከላከል የሚያስችል ሲሆን ያልተለመዱ የአዉታረ-መረብ እንቅስቃሴዎችን ቀድሞ በመለየት እና በመጠቆም በሃገር ላይ ሊደርስ የሚችልን ከፍተኛ ኪሳራ ለመቀነስ ያግዛል።