askwala.com - ለሥራ ቅጥር ቃለ መጠይቅ መለማመጃ የሚውለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት
Header







ለሥራ ቅጥር ቃለ መጠይቅ መለማመጃ የሚውለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

Image name: Google_AI.jpg

ሥራ ፈላጊዎች ከሚያልፉባቸው ሂደቶች መካከል ለቅጥር የሚደረገው ቃለ መጠይቅ ብዙዎችን ያስጨንቃል፡፡
ይህን ጭንቀት የተረዳው ጉግል ከክፍያ ነጻ የሆነ ኢንተርቪው ዋርምአፕ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የድረ-ገጽ መተግበሪያ ማስተዋወቁን ቪ.ኦ.ኤ ዘግቧል፡፡
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተዋቀረው ይህ መተግበሪያ ሰዎች ለሥራ ቅጥር ቃለ-መጠይቅ ከመሄዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ እድል የሚሰጥ ነው፡፡
በተጠቃሚው ምርጫ መሠረት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ፕሮጀክት አስተዳደር፣ ዳታ አናሊቲክስ፣ በድረ-ገጽ ሽያጭ እና ግብይት እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ የሚያጠነጥኑ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎችን ድረ-ገጹ ያዘጋጃል፡፡
ግለሰቡ ለጥያቄዎቹ በድምፅ የሚሰጠውን ምላሽ ድረ-ገጹ በመቅዳት እና ወደ ጽሁፍ በመቀየር መልሶቹን መለስ ብሎ ለመገምገም እድል ይሰጣል፡፡ ከድምፅ ይልቅ ጽሁፍን ምርጫ ላደረጉም አማራጭ አለው፡፡
ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡትን መልሶች ተጠቃሚው በራሱ ከመገምገም ባለፈም በመተግበሪያው የመተንተን እድል አላቸው፡፡
በዚህም ተጠቃሚው የራሱን ግምገማ ከድረ-ገጹ የትንተና ግብረ-መልስ ጋር በማጣመር ለቃለ መጠይቅ ብቁነቱን ደጋግሞ መፈተሽ ያስችለዋል፡፡
ጉገል የውይይት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Conversational AI) ሥርዓቶችን ለማበልፀግ የሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል በመሆን መተግበሪያው መበልፀጉን ዘገባው አመላክቷል፡፡ 

















Short info

× Chat