askwala.com - በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበር ተግባሮች የትኞቹ ናቸዉ?
Header







በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበር ተግባሮች የትኞቹ ናቸዉ?


በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበ ተግባራት በስልኮቻችን አማካኝነት በተጠቃሚዉ ላይ የሚቃጣ የጥቃት አይነት ነው፡፡
የጥቃቱ መነሻም የምንጠቀምባቸዉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከሲም ካርድ ጋር ግንኙነት በሚፈጥርበት ጊዜ እንዲሁም ከበይነመረብ ጋር በሚገናኝበት ወቅት የሚፈጸሙ የማጭበርበር አይነቶች ናቸዉ።
በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ከሚፈጸሙ የማጭበርበሪያ መንገዶች መካከል የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ ፦
 በስልኮቻችን ላይ ያልተሳኩ ጥሪዎችን በማድረግ( (Missed call)የሚፈጸም ማጭበርበር
ይህ አይነት የማጭበርበር ወንጀል መልሰዉ የይደዉሉልኝ ጥሪ በማስመሰል እና ተጠቃሚዎች መልሰው እንዲደዉሉላቸው በማድረግ ያላቸዉን ሂሳብ በሰከንድ የመዉሰድ ስልት ነዉ።
 በአላስፈላጊ መልክቶችን በማጥለቅለቅ የሚፈጸም ማጭበርበር ፦ ይህ ደግም በጣም ብዙ መልክቶችን በመላክ የሚመጣ የማጭበርበር ስልት ሲሆን ከመልክቶችም መካከል እንደ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፣ ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ስኮላርሽፕ እና የመሳሰሉትን መልክቶች በመላክ ደንበኞች መልሰው እንዲልኩ፣ እንዲደዉሉ በማድረግ ሚስጥራዊ መረጃን መመንተፍ፣ ሂሳብን መዉሰድ እና ሌሎችን ድርጊቶች በማድረግ የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል ነዉ።
 በቀጥታ በመደወል / direct call /፦ በቀጥታ በመደወል ከትክክለኛ ሰዉ ወይም ከትክክለኛ ድርጅት እንደተደወለ በማስመሰል የተለያዩ መረጃዎችን/ፋይሎችን/ዶክመንቶችን መስረቅ፣ማንነታችን የማጣራት፣ የተለያዩ ሚስጢራዊ ኮዶችን፣ አካዉንቶችን፣ የይለፍ ቃሎችን የመመንተፍ እንዲሁም በዚህ አካዉንት ብር መላክ አለብዎ ምክንያቱም ስኮላር ደርሶዎታል ፣ ሎተሪ ደርሶዎታል እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመጠቀም የሚፈጸም የማጭበርበር ስልት ነው፡፡ 

















Short info

× Chat