ቴክኖሎጂው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን በጉግል፣ ሞኔል ኬሚካል ሴንስስ ሴንተር በተባለ ተቋም እና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አማካኝነት መበልፀጉን ቪ.ኦ.ኤ ዘግቧል፡፡
“Principal Odor Map” የሚል መጠሪያን በጉግል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪ ቡድን ያገኘው ይህ ሥርዓት የሞለኪውሎችን የሽታ ባሕርያት ለመተንበይ እና አዳዲስ ሽታዎችን ለማግኘት የሚያስችል የሰው ሰራሽ የነርቭ አውታረ መረቦች ስሪት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ ተመራማሪዎቹ የተለያዩ ሞለኪውሎችን የሚወክሉ ስፋት ያላቸው የመዓዛ መግለጫዎችን ያካተተ የዳታ ክምችት ማሰባሰብ መቻላቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ይህን መሰል ቴክኖሎጂ ለጤናው ዘርፍ፣ ለምግብ እና ሽቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የምርምር ቡድኑ ገልጿል፡፡
ለአብነትም ቴክኖሎጂው ከትላልቅ የጤና እክሎች ውስጥ በነፍሳት አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመዋጋት ሊረዳ ይችላል፡፡ ሥርዓቱ አንድ ሞለኪውል የወባ ትንኞችን ከሰዎች በማራቅ ረገድ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ሊለካ እንደሚችል የተመራማሪዎቹ እምነት ነው፡፡