ህብረቱ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል የወሰነው ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ጦርነት እያባባሰች ነው በሚል ምክንያት እንደሆነ የኤኤፍፒ ዘገባ ያመለክታል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን፤ ሩሲያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የዩክሬን ጦርንት ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ አድርጋለች ሲሉ ተናግረዋል።
ማዕቀቡ የነዳጅ ዋጋ ላይ ገደብ ከማድረግ በተጨማሪ የሩሲያ የኤክስፖርት መጠንን ከ7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንዲወሰን የሚያስገድድ ነው ተብሏል።