የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው ከፈቱ፡፡ ሙዚየሙ ሁለት ግዙፍ ህንፃዎች ያሉት ሲሆን በውስጡ ለከባቢ አየር ተጣጣሚ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና ቋሚና ጊዚያዊ ሙዚየሞችን አካቷል፡፡
በእለቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንት ኢንስቲትውት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሌሎች ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን በማቅረብ፤ ክቡር እንግዶችን አስጎብኝተዋል፡፡