askwala.com - በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ የ Rise Ethiopia ጥናት አመላከተ።
Header







በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ የ Rise Ethiopia ጥናት አመላከተ።


በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ የ Rise Ethiopia ጥናት አመላከተ።

በዛሬው እለት Rise Ethiopia ፕሮግራም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አዘጋጅነት በ ሂልተን ሆቴል አየተከሄደ ይገኛል ።

Rise Ethiopia በ World Bank የሚደገፍ እና አለምአቀፍ የምርምር ፕሮግራም ሲሆን በትምህርት ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመ ድርጅት ነው። በዚህም ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቱት በጋራ በመሆን ጥራት እና ምርምሩን የሚያካሄዱ ተቋሟት ናቸው።

የ Rise Ethiopia ዋና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጣሰዉ ወልደሀና አና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮግራሙ አስጀምረዋል።

በኢትዬጲያ በRise አማካኝነት በተለያዩ የአንደኛ ደረጃ 168 ትምህርትቤቶች በሚገኙ በ 9,000 ተማሪዎች በተጠናዉ ጥናት መሰረት 2ኛ ክፍል ተማሪዎች 68% እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች 51% ያህሉ ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ተገልጿል። የተማሪዎችን የትምህርት ዉጤት ለማሻሻል የትምህርት ስርአቱ የተናበበ እና የተቀናጀ ትግበራ አስፈላጊ እንደሆነ በጥናቱ ላይ ተመላክቷል
በ ፕሮግራሙ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ጣሰዉ ወልደሀና እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት በ ትምህርት ዙርያ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚቻል ገልፀዋል።

በጥናቱ ላይ የትምህርት ስርአቱ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላክቷል።

በተጨማሪም በቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ለይ እና ከ 1- 4 ተማሪዎች መሰረታዊ ክሎት እንዲኖራቸው መሰራት አለበት ተብሏል።

ከነዚህም መካከል :-

1.ማንበብ እና መፃፍ
2.ሂሳብ ማስላት
3.የተረጋጋ ስነልቦና እና መልካም ማህበራዊ መስተጋብር ናቸው። 

















Short info

× Chat