በውስጡ ቅባት፣ ፕሮቲን አለው። ካርቦሃይድሬት፣ ቫይታሚን ኤ፣ ዲ ፣ ቢ6 እና ሲ እንዲሁም ማግኒዚየም፣ ብረት ፣ ፋይበር እና ካልሲየም ይዟል፡፡
➡️ከፍተኛ የደም ግፊትን በእጅጉ ይቀንሳል፡- የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ጦስኝ ስብ የጋገሩ የደም ቧንቧዎች በማስፋት ደም ያለምን መጨናነቅ በትቧዎቹ ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ ከፍተኛ የደም ግፊት መቀነሱ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የደም ቅባት መጠን ወይም ኮሌስትሮልንም መቀነሱ ተረጋግጧል፡፡
➡️ ሳልን ያስቆማል፡- ጦስኝን ቀቀል ውሃውን መጠጣት ሳልን ጨምሮ አጣዳፊ ብሮንካይተስ የተሰኘውን የመተንፈሻ አካል ሕመም ያስቆማል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሳል ሳቢያ የሚቆስልን ጉሮሮ ፈውስ ይሰጣል፡፡
➡️የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጎለብታል፡- ጦስኝ በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ጠቃሚ ቫይታሚኖች እንደ ቫይታሚን ሲ፣ኤ እና ዲ የመሳሰሉትን በመያዙ በማንኛውም ጊዜ ቅጠሉን ቀቅለን እንደ ሻይ ብንጠጣ በቀላሉ ጉንፋን ጨምሮ ሌሎች የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን መከላከል ይቻላል፡፡
➡️ፀረ-ሻጋታ ነው፡- በቀላሉ ሊሻጋቱ የሚችሉ እንጀራን ጨምሮ ማናቸውም ነገሮች ላይ የጦስኝ ቅጠል ብናደርግበት ከመሻገት ይድናል፡፡
➡️ጦስኝ ጸረ- ነፍሳት ነው፡- በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ ነፍሳትና ተባዮች ካስቸገራችሁ የጦስኝ ቅጠል ቀቅላችሁ የሚያስቸግራችሁ ቦታ እርጩት፡፡ ውጤቱን በፍጥነት ያዩታል፡፡
➡️ከመልካም ማዕዛው በተጨማሪ ፀረ- ፈንገስና ፀረ-ሕዋሳት ይዘት ስላለው በጥርስ ሳሙናና በገላ ሽቶዎች ውስጥ ሳይቀር በቅመምነቱ በዘመናዊ መልኩ ይገባል፡፡
➡️ስሜታችንን (mood) ከፍ ለማድረግ ይረዳል፡- ጦስኝ በውስጡ የያዘው Carvacrol የተሰኘው ንጥረ ነገር የአእምሮችን ሕዋሳትን በማነቃቃት ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
➡️ጥሩ የምግብ ምንጭ ነው፡- በፈረንሳይና በጣሊያን አገራት እና በአብዛኛው ሜዲትራኒያን አካባቢ እንዲሁም በኛ ሀገርም ጦስኝ የተለያዩ ስጎዎችን ለመስራት ያገለግላል፡፡
➡️ለብጉር ማጥፊያነት ያገለግላል፡- ፀረ-ባክቴሪያ ንጥረነገር ስላለው ከብዙዎቹ ያለሐኪም ትዕዛዝ ከሚሸጡ ዘመናዊ የቡግር ማጥፊያ መድኃኒት የተሻለ ነው፡፡ እርጥቡን ጦስኝ ወቅጦ በብጉሩ ላይ ለተወሰነ ሰዓታት በማስቀመጥ መታጠብ ጥሩ ውጤት ያስገኛል::
© EthioTena