AskwalaToday is Jummah. Happy Jummah, Happy friday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!


                                     

Welcome to askwala!


Inform          Today is Friday, October 02, 2020

ከአምስት ዓመት በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኃይል ተጠቃሚ ይሆናሉ

Informed yesterday at 04:43 PM

ከአምስት ዓመት በኋላ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ተገለጸ።
በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ‘የኤሌክትርክ ዘርፍ ሪፎርም ፍኖተ ካርታ’ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጀነር ስለሺ በቀለ እንዳሉት ኢትዮጵያ በኃይል ዘርፍ ልማት እጅግ ኋላ የቀረች አገር ናት።
“ከ110 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት አገር በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ ከ4 ሺህ 5 ሜጋ ዋት የማይበልጥ ኃይል እያመረተች ትገኛለች” ብለዋል።
ከአፍርካ አገራት ጋር ስትነጻጸር እጅግ ኋላ የቀረችና 60 ሚሊዮን ሕዝቧ ዘመናዊ የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ እንዳልሆነም ይገልጻሉ።
በዝግጅት ላይ የሚገኘው ፍኖተ ካርታ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ሁሉም የአገሪቷ ሕዝብ ኃይል እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑንም ነው ኢንጀነር ስለሺ የገለጹት።
“በፍኖተ ካርታው ትኩርት ከተሰጣቸው መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያለበት እዳ እንዲቃለል መንገዶችን ማመቻቸት አንዱ ነው” ብለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ካለበት 370 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ ግማሹ በገንዘብ ሚኒስቴር ስር አዲስ ለሚቋቋመው የንብረትና የዕዳ ማኔጅመንት ኩባንያ እንዲተላለፍ መወሰኑን አስረድተዋል።
“ይህ መንገድ ዘርፉ በተሻለ መልኩ ከችግር ወጥቶ ለኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ስኬት እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል” ብለዋል።  


በዋቄፈና እምነት ሀጥያት፣ ገነትና ገሃነም አሉ?

Informed 2 days ago

Informer:  BBC News Amharic
በቀደምቱ የኦሮሞ ሕዝብ እምነት፤ የእምነቱ ተከታዮች ሁሉን በፈጠረ አንድ አምላክ ያምናሉ።
የእምነቱ ተከታዮች "ፈጣሪ ስሙ መቶ ነው፣ ሆዱ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ፣ ሃሳቡ ደግሞ ንጹህ ነው" ይላሉ።  


በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አማካኝነት የተገነባው ትምህርት ቤት።

Informed 3 days ago

በቦረና ዞን በዱቡሉቅ ወረዳ የሚገኝ ትምህርት ቤት ነው ትምህርት ቤቱ ግድግዳው ከእንጨት፣ ጣሪያው ደግሞ በላስቲክ የተሸፈነ፤ የተገነባውም በአካባቢው ህብረተሰብ ተሳትፎ ነበር።
ጣሪያውም የሚያፈስ ፣ ለተማሪዎች የሚሆን መቀመጫ ያልተሰራለት ስለነበር ተማሪዎች ይቀመጡ የነበረው በዱካ በተገኘው ነገር ላይ ነው።
ባለፈው ዓመት ይህን ትምህርት ቤት የሚያሳይ ምሰል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ምስሉን ተቀባበሉት።
ምስሉ ከተሰራጨ በሃላ በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ የሚገኙ ሰዎች ትምህርት ቤቱን ለማደስ ባደረጉት እርብርብ በአጭር ጊዜ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ብር ተሰበሰበ።
አሁን ያ ደሳሳ ጎጆ ትምህርት ቤት በአዲስ ተተክቶ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቷል። ለግንባታውም አንድ ሚሊዮን የሚሆን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ ገንዘቡም በፌስቡክ በኩል በተደረግው ጥሪ የተሰበሰበ ነው።
አሁን ተማሪዎች ፀሀይ እና ዝናብ ሳይነካቸው የመቀመጫ ወንበር ላይ ሆነው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ። ይህ ሁሉ የሆነው በህብረተሰቡ ተሳትፎ ስለሆነ በዚህ ተግባር ላይ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ይገባል።
በፌስቡክ እንዲህ አይነት መልካም ስራዎችን፣ የኅብረተሰቡን ችግር የመቀርፍና በቋሚነት የሚያገለግል ስራዎችን መስራት እንደሚቻል ያሳየ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ የለውጥ መሰረት እንደሆነ ያስመሰከረ ተግባር ነው።
ማህበራዊ ሚዲያን ማህበረሰብን የሚጠቅም ነገር ለመስራት፣ ለመማሪያና ለበጎ አድራጎት ስራ እንጠቀምበት! !  


የኮሪያ ቋንቋና ባህልን በኢትዮጵያ የሚያስተምር “ኪንግ ሴጆንግ ኢንስቲትዩት” በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተከፈተ፡፡

Informed 3 days ago

የኢንስቲትዩቱ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በ14/1/2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በተከናወነበት ወቅት በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የኪንግ ሴጆንግ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኩ እን ጆንግ እንደገለፁት፣ ኪንግ ሴጆንግ ኢንስቲትዩት ለተለያዩ ሀገራት ዜጎች የኮሪያ ቋንቋና ባህልን ለማስተዋወቅ ሲባል በኮሪያ መንግሥት እ.ኤ.አ. በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ መንግሥታዊ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፣ ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ ደረጃ ለአምስተኛ ጊዜ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መከፈቱን ይፋ አድርገዋል፡፡
የኪንግ ሴጆንግ ኢንስቲትዩት በአሁኑ ጊዜ በ76 ሀገራት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ በአፍሪካ ማለትም በናይጄሪያ፣ በግብጽ፣ በቦትስዋና እና በኬኒያ ሀገራት ብቻ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ፣ ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ በተለይም በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ እንዲከፈት ሙሉ ድጋፍ ላበረከቱት ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነ መስቀል ጠና እና በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ለሆኑት ሊም ሆዎን ሚን ጥልቅ የሆነ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ የኪንግ ሴጆንግ ኢንስቲትዩት በአብዛኛው የኦንላይንና የኦፍላይን ትምህርት መስጠት መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡  


የአለም ሙቀት መጨመር እንሰሳቱን እየፈተነ ነው

Informed 4 days ago

ለአለም ሙቀት መጨመርና ለአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጆች በየጊዜው የሚያደርጉት የደን ጭፍጨፋና የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀት ዋናው ምክንያት ነው፡፡ ታዲያ ይህ የአየር ንበረት ለውጥ የሰው ልጆችን ከመጉዳት አልፎ በምድር ላይ ለሚኖሩ ፍጠረታት ሁሉ ጉዳቱ ከፍተኛ ሆኗል፡፡ የዚህ ጉዳት ከሰው ቀጥሎ ዋና ተጠቂ እንሰሳት መሆናቸውን በየጊዜው የሚከሰቱ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ማሳያ ናቸው፡፡
በተለይም የአየር ንበረት ለውጡ ያስከተለው የሙቀት መጨመር እንሰሳቱ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል፡፡ የሚኖሩበትን አካባቢ ከማስለቀቅ አልፎ ለሞት እየዳረጋቸው መሆኑን በየጊዜው የምንሰማቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በሙቀት መጨመሩ የተቸገሩት የታንዛኒያ ጉማሬዎችም በጭቃ ውስጥ እራሳቸውን በመክተት ሰውነታቸውን እያቀዘቀዙ እንደሚገኙ የሲጂቲኤን ዘገባ ያሳያል፡፡
ዘገባው አንዳሳየው በመቶዎች የሚቆጠሩ የታንዛኒያ ጉማሬዎች በቀዝቃዛ ጭቃ ውስጥ ተሰብስበው በመግባት ራሳቸውን በማቀዝቀዝ፤ በማዝናናት ሙቀቱን ለመቋቋም እየታገሉ ነው፡፡
በቀዝቃዛ ጭቃ ውስጥ መንከባለላቸው ከመጠን በላይ ሙቀጥ እንዳይሰማቸውና በሙቀት ከማቃጠል እንደሚከላከልላቸው ነው ያመለከተው፡፡
እንሰሳቱ ያለቸውን አመራጭ በመጠቀም ራሳቸውን ከሞት ለመታደግ እየጣሩ ባለበት በዚህ ወቅት የምናደርገው የአካባቢ ጥበቃ ተግባር ሚነው የጎላ መሆኑ እሙን ነው፡፡  


LET THERE BE!

Informed 4 days ago

Informer:  Appeal For Purity
Whenever I think about my salvation, I think about this verse:
"Then God said, “Let there be light”; and there was light." Genesis 1:3 NASB

Before God calls light over the earth, the earth was covered with darkness: "The earth was formless and void, and darkness was over the surface of the deep" Genesis 1:2a NASB  


በያዝነው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ ተገለፀ

Informed 2 weeks ago

በኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል አስጠነቀቀ፡፡
ማዕከሉ እንደገለጸው በተለይም በመካከለኛው እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል፡፡
በእነዚህ ሀገራት የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ የልህቀት ማዕከሉ አስጠንቅቋል፡፡
የዝናብ ትንበያው ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጠሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሚጠበቅ ሲሆን በምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡  


እስራኤል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ዳግም በሯን ልትዘጋ ነው

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
እስራኤል የአይሑድ አዲስ ዓመት ከመግባቱ በፊት እየተስፋፋ ያለውን ኮሮና ለመመከት ጥብቅ እርምጃዎችን ልትወስድ ነው፡፡ ጥብቅ ብሔራዊ ውሸባ እንደሚኖርም ይፋ አድርጋለች፡፡

ከሚቀጥለው አርብ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው አዲስ መመርያ ለሦስት ሳምንታት ይዘልቃል፡፡ ናታንያሁ እርምጃው ‹‹ሁላችንንም ከባድ ዋጋ ያስከፍለናል ነገር ግን ማድረግ አለብን›› ብለዋል፡፡ እስራኤል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀን በአማካይ በቫይረሱ የሚያዙባት ዜጎች ቁጥር 4ሺ በመድረሱ ድንጋጤ ተፈጥሯል፡፡  


የሃይማኖት አባቶች ‘እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ’ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ

Informed 3 weeks ago

የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ‘እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ’ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ።
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹ አቡነ ማቲያስ አዲሱን አመት አስመልክተው ባስተላለፉት የ’እንኳን አደረሳችሁ’ መልእክት ”አዲሱን አመት አንድ ብለን ስንጀምር ያለፈውን ዓመት ለአፍታ ቆም ብለን ማሰብ የሚኖርብን ነው” ብለዋል።
ባለፈው አመት የተከሰቱትን ድክመቶች በአዲሱ ዓመት ላለመድገም ቁርጥ ውሳኔ በማሳለፍ ወደ ስራ መግባት የሚያስፈልግበት እንደሆነ አመልክተዋል።  


የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጡረታ ለተሰናበቱ የቀድሞ ሰራተኞቹ ለበአል የሚሆን ሰጦታ አበረከተ።

Informed 3 weeks ago

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በጡረታ ለተሰናበቱ የቀድሞ ሰራተኞች በመኖሪያ ቤትታቸው በመገኘት ለበአል የሚሆን ሰጦታ ያበረከቱ ሲሆን ስጦታዉ ለምግብነት የሚውሉ እንደ ዘይት፣ ምሰር፣ ሩዝ ና ፓሰታ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዉ የተመረተ የፊት ጭምብል ና ሳኒታይዘርን ያካተተ ነው።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬዉ ተገኘ በስጦታው ስነ-ስርአት ድጋፍ ለተደረገላቸው የቀድሞ ሰራተኞች የጤና ችግር ሲኖርባቸው በዩኒቨርሲቲዉ የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታል የነፃ ሕክምና እንደተመቻቸላቸዉ አረጋግጠዉላቸዋል።  


ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ

Informed 3 weeks ago

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾሙ።
ሹመቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።  


የኤርትራ መንግሥት በሃይማኖታቸው ምክንያት ያሰራቸውን 20 ያህል ግለሰቦች ለቀቀ

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
የኤርትራ መንግሥት በእምነታቸው ምክንያት ለዓመታት አስሯቸው የነበሩ ከ20 በላይ ግለሰቦችን መለቀቁን የተለያዩ ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ።
ታሳሪዎቹ አብዛኞቹ ከወንጌላውያን እና ጴንጤቆስጣል ቤተ እምነቶች እንደነበሩ ጨምረው አረጋግጠዋል።
ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል የተወሰኑትም ከአስመራ ውጪ ታስረው መቆየታቸው ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያሳያል።  


HAPPY ETHIOPIAN NEW YEAR!

Informed 3 weeks ago

Informer:  Appeal For Purity
Happy Ethiopian New Year’s Day!

This
is going to be 2013, according to an Ethiopian Calendar!
May this year be a year of peace, love and prosperity to Ethiopia and to all Ethiopians.

And guess what? Today is my birthday. Yep! I was born on this day: መስከረም አንድ (Meskerem 1). And that is why they called me Meskerem.

Happy Birthday to me and to all who were born on this day!  


የ86 አመት የእድሜ ባለፀጋ አያት መደፈር መላ ህንድን አስደንግጧል

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
በህንዷ መዲና ደልሂ የ86 አመት እድሜ ባለፀጋ አያት መደፈራቸውን ህንድን አንቀጥቅጧታል። የእድሜ ባለፀጋዋን በመድፈር በ30ዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ግለሰብ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።
ግለሰቧ በዚህ ሳምንት ሰኞ እለት ወተት የሚያመጣላቸውን ሰው እየጠበቁ ባለበት ወቅት ጥቃት እንደደረሰባቸው የደልሂ የሴቶች ኮሚሽን ስዋቲ ማሊዋል ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"ጥቃት አድራሹ ወተት የሚያመጣላቸው ግለሰብ እንደማይመጣና ወተት የሚመጣበት ስፍራ ልውሰድዎት አላቸው" ብለዋል።
"እያለቀሱም እንዲተዋቸው ለመኑት። አያቱ ማለት እንደሆነም ተማፀኑት። ግን ልመናቸውም ሆነ መማፀናቸው ትርጉም አልነበረውም። ራሳቸውን ለመካለከልም ሲታገሉ ክፉኛ ድብደባ ፈፅሞባዋቸዋል። ከዚያም ደፈራቸው" ብለዋል።  


በመዲናዋ በኮሮና ቫይረስን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

Informed 3 weeks ago

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።  


ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.